በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት በትግራይ ክልል


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኮቪድ-19 ክትባት ሊሰጥ ነው። በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በመቀሌ ከተማ የተጀመረውን ክትባት በትግራይ ክልል ሁሉም አካባቢዎች ለማስፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ሲገለጽ በጤና ቢሮው የኮቪድ-19 መከላከያ ሃላፊ ዶ/ር አርነት አዳነ እንዳሉት፤ ለክትባት አገልግሎት የሚውል 108 ሺህ ዶዝ መድሐኒት ከጤና ሚኒስቴር ለክልሉ ተልኳል።

በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ሁሉም የጤና ተቋማት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ክትባት መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።

የክትባት ዘመቻ በሽሬእንዳስላሴ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ፍሬወይኒ፣ ማይጨውና አዲሽሁ ከተሞች በተያዘው ወር ውስጥ እንደሚቀጠል አስታውቀዋል።

በመቀሌ ከተማ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱ እንደተሰጠ ወደ ክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ለማስፋት ተጨማሪ የክትባት መድሐኒት ከጤና ሚኒስቴር እየተጠበቀ መሆኑን፤ የክትባት መድሐኒት ማቆያ ፍሪጅ ዝግጅትና የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚካሄድ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG