በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ መከላከል ይቻል ነበር"- አጣሪ ኮሚቴ


የኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ያስከተለውን ቀውስ መከላከል ይቻል ነበር ሲል የወረርሽኙን አመጣጥ እና የተሰጠውን ምላሽ የመረመረው ነጻ አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት አቀረበ።

ኮሚቴው ዛሬ ረቡዕ ባወጣው ሪፖርቱ ወረርሽኙን ያባባሰው የዓለም የጤና ድርጅት ዝግተኝነት እና ድክመት እንዲሁም ለጉዳዩ በቂ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ አመራር ትኩረት አለመሰጠቱ መሆኑን ጠቁሟል።

ዓለም አቀፍ ወረርሽኞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ለዓመታት ማስጠንቀቂያዎች ሲወጡ እንደነበር የጠቀሰው የመርማሪ ኮሚቴው ሪፖርት ቻይና ዉሃን ከተማ የየህክምና ባለሙያዎች የወረርሽኝ አደጋ መደቀኑን አስቀድመው ቢያስጠነቅቁም ያን መረጃ ተምርኮዞ እርምጃ አልተወሰደም ብሏል።

በሽታውን ለመዋጋት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ አመራርም አልነበረም ያለው ነጻው መርማሪ ኮሚቴ የነበሩት ውጥረቶች ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ሆኑ የተለያዩ ተቋማት ወረርሽኙን በተቀናጀ መንገድ ለመታገል ጥረት ቢያደርጉም እንቅፋት እንደደቀኑባቸው አውስቷል።

XS
SM
MD
LG