በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሃምሳ ሀገሮች ተዛምቷል


መጀመሪያ ህንድ ውስጥ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ሃገሮች መዛመቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለሙ ድርጅት የህንዱ የቫይረሱ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት ደቅኗል ሲል ትናንት ማስታወቁ ይታውሳል።

ህንድ ዛሬ ብቻ 4,205 ሰዎች በኮቪድ--19 ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህ እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገበው አሃዝ ከፍተኛው ነው። አጠቃላዩ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ250,000 አልፏል።

በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ23 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን ዛሬ ብቻ 348,420 ተያዦች ተገኝተዋል። እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው ዕለታዊ የአዲስ ተጋላጮች ቁጥር መሆኑ ታውቋል።

በህዝብ ብዛት ሁለተኛ በሆነችው ሃገር ኮቪድ-19 እጅግ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሯል። የህንዱን የበሽታው ስርጭት መክፋት ተከትሎ የዓለም ቀይ መስቀል ፌዴሬሽን የኮቪድ-19 ተግላጮች ቁጥር በመላ እስያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን አስገንዝቧል።

በሁለቱ ሳምንት ውስጥ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር በ5 ነጥብ 9 ሚሊዮን መጨመሩን ያስታወቀው ቀይ መስቀል አሃዙ በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ በአፍሪካ እና በጠቅላላ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከተመዘገበው ቁጥር እንደሚበልጥ ጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG