በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘሚ የኑስ በኮቪድ-19 አረፉ


የጆይ ኦቲዝም ማዕከል እንዲሁም የኒያ ፋውንዴሽን መስራች እና ሥራ አስኪያጅዋ ወይዘሮ ዘሚ የኑስ

በእንግሊዝኛ ኦቲዝም ተብሎ ለሚጠራው የአእምሮ ሥራ ሂደት መዛባት ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ልጆች ተሟጋችነታቸው እና ባደረጉትም ድጋፍ እጅግ ታዋቂ የሆኑት ወይዘሮ ዘሚ የኑስ በኮቪድ-19 ሳቢያ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።

የጆይ ኦቲዝም ማዕከል እንዲሁም የኒያ ፋውንዴሽን መስራች እና ሥራ አስኪያጅዋ ወይዘሮ ዘሚ የኑስ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም የኮቪድ-19 ጽኑ ህክምና ማዕከል ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ማረፋቸው ታውቋል።

ወ/ሮ ዘኒ የአዕምሮ ዕድገት ዝግመት እክል ተጋላጭ ከሆነው ወንድ ልጃቸውን በመንከባከብ ባገኙት ዕውቀት እና ተመክሮ ህብረተሰቡም በጥልቀት ግንዛቤ እንዲኖረው እና ለተመሳሳይ ችግር የተጋለጡ ሌሎች ልጆችም ድጋፍ እንዲያገኙ ለአያሌ ዓመታት በትጋት ሲሰሩ ኖረዋል።

XS
SM
MD
LG