በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአክሱም ጉዳይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገለፀ


ፎቶ ፋይል፦ አክሱም ከተማ

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ህዳር 19 /2013 ዓ.ም በተካሄደ ውጊያ “በውጊያው የተሳተፉ 93 ሰዎች የወታደር የደንብ ልብስ ያልለበሱ ሞተዋል” ሲል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገልጿል።

“ከተማው ውስጥ በመከላከያ ሠራዊትና በኤርትራ ወታደሮች ንፁሀን ተገድለዋል” ተብሎ የቀረበውን ክስ መሥሪያ ቤታቸው ለሁለት ወር ገደማ ሲመረምር መቆየቱን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ዛሬ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

"እስካሁን ባለው የተጣራ መረጃ መሠረት ስድስት ስዎች በመከላከያ ሠራዊቱ መገደላቸውን” ማረጋገጣቸውን አቶ ፍቃዱ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ግን በተመሳሳይ ጊዜ አክሱም ከተማ ውስጥ በተካሄደ ውጊያ “በመቶዎች የሚቆጠሩ” ሰዎች በተቀነባበረ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቀደም ሲል ባወጣው ሪፖርት ጠቁሞ ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በአክሱም ጉዳይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:16 0:00


XS
SM
MD
LG