በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ ውስጥ እየተዛመተ ያለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢነት


የጤና ባለሞያዎች በህንድ

ህንድ ውስጥ እየተዛመተ ያለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

በዓለም የጤና ድርጅት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተያያዥ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዳይሬክተሯ ዶ/ር ማሪያ ቫን ኬርኮቭ የተጠቀሰውን የቫይረሱ ዝርያ በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ ባደረጉት ገለፃ፣

"ይህ ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ብለን ፈርጀነዋል። ቫይረሱ በይበልጥ እየተዛመተ መሆኑን የሚጠቁሙ ማስረጃዎች አሉ" ብለዋል።

ፊሊፒንስ በዚህ ህንድ ውስጥ እየተዛመተ ባለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ የተያዙ የመጀመሪያ ሁለት ተጋላጮች አግኝተናል ብላለች። ሁለቱ ሰዎች በቅርቡ ወደ ኦማንና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተጉዘው ወደፊሊፒንስ የተመለሱ መሆናቸውን አስታውቃለች።

ህንድ ውስጥ ዕለታዊ የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር በጥቂቱ ቢቀንስም አሁን እጅግ በበዛ ቁጥር እየተዛመተ ነው። በዛሬ ዕለት ብቻ ሦስት መቶ ሠላሳ ሺህ አዲስ ተያዦች መገኘታቸው ተግልጿል። ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰዎች ሞተዋል።

XS
SM
MD
LG