በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሌ ክልል 7 የምርጫ ክልሎች ላይ የመራጮች ምዝገባ ተቋረጠ


ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ
ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ

ምርጫ ቦርድ ለአምስት ሴናተሮች አስተያየት ምላሽ ሰጠ

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በሶማሌ ክልል ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ተቀብሎ በ7 የምርጫ ክልሎች ላይ የመራጮች ምዝገባ እንዲቋረጥ ወስኗል። ቦርዱ 5 የአሜሪካ ሴኔት አባላት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ዝግጅት እየተደረገበት ያለውን ምርጫ በተመለከተ ያወጡትን መግለጫም ትክክለኛውን የምርጫ ዝግጅት ሂደት የማያንጸባርቅ ነው ብሎታል።

በሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ ላይ ቅሬታ በቀረበባቸው 7 የምርጫ ክልሎች ላይ የምዝገባው ሂደት ተቋርጦ አስፈላጊው ማጣራት እንዲካሄድ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ወሰነ። የክልሉ ዋና ከተማ ጂጂጋን ጨምሮ ጎዴና ቀብሪደሃርም ምዝገባው ከተቋረጠባቸው ምርጫ ክልሎች መካከል ናቸው።

የአሜሪካ ድምጽ ከዚህ በፊት በሶማሌ ክልል ያሉ ተቃዋሚዎች በመራጮች ምዝገባ ላይ ያላቸውንቅሬታ ዘግቦ የነበረ ሲሆን ቅሬታውን ያቀረቡትን ኦብነግን፣ ኢዜማን፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲንና የግል እጩዎችን ምርጫ ቦርድ አዲሰበባ ጠርቶ አነጋግሯቸው ነበር።

የውሳኔው መነሻም ይህንን ንግግር ተከትሎ ቦርዱ ያደረጋቸው ማጣራቶች መሆናቸውን የምርጫ ቦርድ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሶሊያና ሽመልስ ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በሶማሌ ክልል 7 የምርጫ ክልሎች ላይ የመራጮች ምዝገባ ተቋረጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00


XS
SM
MD
LG