በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ደቡብ ወሎ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ ከኦሮምያና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ ወደ ደቡብ ወሎ የሚገቡት ተፈናቃዮች ብዛት እየጨመረ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ፡፡

ዞኑ አራት ሳምንታት ባለሞላ ጊዜያት ውስጥ ብቻ ከ8 ሽህ በላይ ተፈናቃዮችን ተቀብሏል፡፡ እስካሁን 18 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የምግብ፣ የአልባሳትና የገንዘብ ድጋፍ በመንግሥት፣ በውጭ አገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ በአካባቢው ኗሪዎችና በባለሃብቶች ተደርጓል፡፡

በጊዜያዊ መዋጮና የእለት ደራሽ ድጋፍ ተፈናቃዮቹን በዘላቂነት ማቋቋም አይቻልም የሚለው የዞኑ አስተዳደር የፌዴራሉም ሆነ የክልሉ መንግሥት በዚህ በኩል ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የክለልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን 878ሽህ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ መፈናቀላቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ወደ ደቡብ ወሎ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00


XS
SM
MD
LG