በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማልያ ከኬንያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አደሰች


የሶማልያ ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትር አብዲራህማን ዩሱፍ አላዳላ

ሶማልያ ከአጎራባቿ ኬንያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ማደሷን አስታወቀች።

ሁለቱ ሀገሮች ባለፈው ዓመት የተቋረጠውን ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ ካታር የሽምግልና ሚና መጫወቷን ሶማልያ አስታውቃለች።

የሶማልያ ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትር አብዲራህማን ዩሱፍ አላዳላ ትናንት በመግለጫቸው ፌዴራል መንግሥታቸው ለመልካም ጉርብትና ሲል ከኬንያ ጋር የወዳጅነት ግንኙነታችንን አድሷል ብለዋል።

ግንኙነታችንን ለማደስ የተስማማነው አንዱ የሌላኛውን ሉዓላዊነት የማክበር፣ በውስጥ ጉዳይ ያለመግባት፣ የዕኩልነት እና የጋራ ጥቅምና በሰላም አብሮ የመኖር መርህን በተመረኮዘ መንገድ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG