በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ ፌስቡክ ታግዶ እንዲቆይ ፀደቀ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

ፌስቡክ ኩባኒያ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በፌስቡክና ኢንስታግራም ገፆቻቸው ላይ ይዘቶችን ወይም መልዕክቶችን እንዳያስቀምጡ ላልተወሰነ ጊዜ የጣለባቸውን እገዳ የኩባኒያው የቁጥጥር ቦርድ አፅደቀው።

ነፃ አካል እንደሆነ የሚነገረው ይህ ቦርድ የህግ ምሁራን፣ የሰብዓዊ መብት አዋቂዎችና ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሃያ አባላት ያሉት መሆኑ ተገልጿል።

የቦርዱ አምስት አባላት ያሉበት ኮሜቴ ያሳለፈውን ውሳኔ በአብላጫ አባላቱ መጽደቅ ያለበት መሆኑና ከጸደቀ እርምጃው ህግን የሚተላለፍ እስካልሆነ ድረስ ኩባኒያው የቦርዱን ውሳኔ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት ተገልጿል።

የፌስቡክ የቁጥጥር ቦርድ ተልዕኮው በኢንተርኔት መገናኛ መረብ ከሚወጡ ይዘቶች የትኞቹ መወገድ አለባቸው፣ የትኞቹ መነካት የለባቸውም፣ ምክንያቱስ? በሚል ለሚነሱ እጅግ ከባድ የሆኑ በኢንተርኔት ሃሳብን በመግለጽ መብት ጋር ተያያዥ ለሆኑ አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ መስጠት መሆኑን ይናገራል።

ፌስቡክ የቀድሞውን ፕሬዚደንት ያገዳቸው እአአ ጥር ስድስት ቀን የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት የፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ውጤት ማረጋገጫ ለመስጠት ጉባዔ ላይ እያሉ የእርሳቸው ደጋፊዎች ምክር ቤቱ ወርረው ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ ደጋፊዎቻቸው ጥቃቱን በማድረስ ላይ እያሉ ፕሬዚዳንቱ

“በፕሬዚደንታዊ ምርጫው የተሰጠው ድምጽ ተሰርቋል” የሚለውን የሀሰት ውንጀላቸውን በተከታታይ በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው ካወጡ በኋላ ኩባኒያው እንዲታገዱ ውሳኔ ሰጥቷል።

XS
SM
MD
LG