ድሬዳዋ —
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ግማሽ ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። ማህበሩ በመቀሌ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመጠቀሚያ ጊዜአቸው ያለፈ ዘይትና ስንዴ አቅርቧል የሚለውን ወቀሳም መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በደቡብ ክልሎች በልዩ ልዩ ግጭቶች ተጎጂ ለሆኑ ግማሽ ሚሊዮን ዜጎች ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረጉን የማህበሩ ህዝብ ግንኙነት ዶክተር ሰለሞን አሊ ለቪኦኤ አስታወቁ።
ከግጭት ጋር ባልተያያዘ መደበኛ አገልግሎቱ ከ10 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ እንዳደረገ የገለጹት ህዝብ ግንኙነቱ የግጭት ሰለባዎችን ግን ለሌሎች ጉዳዮች ይዟቸው የነበሩ በጀቶችን ሁሉ በማጠፍ ለመደገፍ ጥረት ማድረጉን ነው ዶክተር ሰለሞን የገለጹት።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡