በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ወደ ለንደን ተጓዙ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከጂ ሰባት አባል ሃገሮች አቻዎቻቸው ጋር ለመነጋገር ወደ ለንደን ተጓዙ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከጂ ሰባት አባል ሃገሮች አቻዎቻቸው ጋር ለመነጋገር ወደ ለንደን ተጓዙ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከጂ ሰባት አባል ሃገሮች አቻዎቻቸው ጋር ለመነጋገር ወደ ለንደን ተጉዘዋል። ለሦስት ቀናት በሚካሄደው መደበኛ ስብሰባ እና ከጉባዔው ውጭም በሚካሄዱ ውይይቶች ከሚነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሩስያ እና ቻይና የሚመለከቱ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ዛሬ ማታ እራት ላይ በሚያካሂዱት ውይይት በቅርብ ዓመታት የኒው ክሊየር መርሃ ግብሮቻቸው የድርድር ትኩረቶች ሆነው የቆዩት ሁለት ሃገሮች ኢራን እና ሰሜን ኮሪያን እንስተው እንደሚነጋገሩ ታውቋል። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ጋር የተገናኙት የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቹንግ ኢዩ ዮንግ በሰጡት ቃል

"ዩናይይትድ ስቴትስ ሰሜን ኮሪያን የሚመለከተውን ፖሊሲዋን መገምገሟን ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ከሀገራችሁ ጋር ጉዳዩን በጥልቅ የሚዳስስ ውይይት ለማድረግ እድል በማግኘታችን እናመሰግናለን" ብለዋል።

የባይደን ባለፈው ዓርብ በሰጠው መግለጫ ሰሜን ኮሪያን እስመልክቶ ከድብቋ ኮሙኒስት ሃገር ጋር ለመነጋገር በሩን ክፍት ያደረገ ስትራተጂ እንደሚከተል ይፋ አድርጓል።

ከጃፓን አቻቸው ቶሲሚቱ ሞቴጊ ጋርም የተወያዩት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ሁለቱ ሃገሮች የሰሜን ኮሪያን የኒው ክሊየር እና የተወንጫፊ ሚሳይል ፕሮግራሞች አስመልክቶ የጋራ ስጋት ያላቸው መሆኑን ገልጸው በመሆኑን ከደቡብ ኮሪያ ጋር በመተባበር ጉዳዩን ለመፍታት ቁርጠኞች ነን ብለዋል።

ሚኒስትር ብሊንከን ከብሩናይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዳቶ እርይዋን ዮሶፍ፥ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራሃማንያም ጃይሴንካ እንዲሁም ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ጋር የሚነጋገሩ ሲሆን ሁለቱ ሚኒስትሮች አፍጋኒስታን፥ ኢራን ፥ ቻይናን እንዲሁም ንግድ በተመካለቱ ጉዳዮች እንደሚወያዩ ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG