በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትግራይን አስግቷል ስለተባለ የረሃብ አደጋ  ግንዛቤ መፍጠሪያ ዝግጅት ተከናወነ  


.
.

እኤአ በ1985 ዓመተ ምህረት በዚህ ሳምንት ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ ለመመከት ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት We are the world የሙዚቃ አልበም የተለቀቀው። አልበሙን ተከትሎ በተሰናዳው የሙዚቃ ዝግጅት መላ ዓለም የተረባረበበት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ተከናውኗል።

ከ36 ዓመታት በኃላ የዚህን ዓለም አቀፍ ርብርብ ትውስታ ተንተርሶ፣ በትግራይ ክልል ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለዓለም ለማሳወቅ ያለመ የበይነ መረብ ዝግጅት ከሰሞኑ ተደርጓል።የድጋፍ ማሰባሰብ መርሀግብርን ያከተተው ዝግጅት የተሰናዳው የትግራይ ተወላጆች በሆኑ ወጣቶች እና የትግራይ ዲያስፖራ ማህበራት ትብብር ነው።

“We are the world 36 for Tigray” በተሰኘው ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ በጦር መሳሪያነት እየዋለ ነው የሚል ሙግትም ተነስቷል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለማንሳት ሀብታሙ ስዩም ከዝግጅቱ ጽንሰሀሳብ አመንጭ ዶ/ር ሙሉጌታ ገ/እግዚሃብሄር ጋር በስልክ አጭር ቆይታ አድርጓል።

ትግራይን አስግቷል ስለተባለ የረሃብ አደጋ ግንዛቤ መፍጠሪያ ዝግጅት ተከናወነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:20 0:00XS
SM
MD
LG