በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ህንድ ውስጥ ተባብሶ እየተዛመተ ነው።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ህንድ ውስጥ ተባብሶ እየተዛመተ ነው።

ህንድ ውስጥ ተባብሶ እየተዛመተ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያስከተለውን ለማመን የሚያዳግት ቀውስ አፍሪካ በቅርበት እየተከታተለች ናት ሲሉ የአህጉሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ።

የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጠጠሪያና መከላከያ ማእከል /አፍሪካ ሲዲሲ/ ሥራ አስኪያጅ ጃን ኢንኬንጋሶንግ ሲናገሩ በህዝብ ብዛት የህንድን የሚያክል ህዝብ ያላት አህጉረ አፍሪካ በዚያ ላይ የተዳከመ የጤና ሥርዓት ያላትም እንደመሆኗ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት ስለሚችል እጅግ በጣም መዘጋጀት ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ሃገሮች ከህንድ የሚጠብቁት የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት ሃገሪቱ በወረርሽኙ ምክንያት በገጠማት ቀውስ የተነሳ መዘግየቱ እንዳሳሰባቸውም የአፍሪካ ባልሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

ለበርካታ የዓለም ሃገሮች የኮቪድ-19 ክትባት ለሚያቀርበው ኮቫክስ በሚል አህጽሮት ስም የሚጠራው ዓለም አቀፍ መርሃ ግብር የአስትራ ዜኒካ ክትባቶችን የሚያመርትለት ዘ ሲረም ኢንስቲዩት የተባለው የህንድ ተቋም ነው።

ህንድ ውስጥ በቀኑ የሚመዘገበው አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ቁጥር ወደ 400,000 እየተቃረበ ነው። ዛሬ 386 452 ሰዎች መመዝገባቸውን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከ300,000 በላይ ሲመዘገብ የዛሬው ለዘጠነኛ ጊዜ ነው።

አንዳንድ የሀገሪቱ የጤና አዋቂዎች አሃዙ በይፋ ከሚገለጸውይበልጣል ማለታቸውን ዘገባዎች ጠቅሰዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከሌሎችም ሃገሮች የተላኩ የህክምና እርዳታዎች ዛሬ ህንድ ገብተዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓ ዳይሬክተር ሃንዝ ክሉገ በበኩላቸው የግል ጥንቃቄ ርምጃዎች ሲላሉ ህዝብ በብዛት ሲሰባሰብ፣ የበለጠ ተዛማች የሆነ የቫይረስ ዓይነት ሲከሰት እና ክትባት ያገኘው ህዝብ ብዛት ዝቅ ያለ ሲሆን ህንድ ውስጥ የደረሰው ሁኔታ በየትኛውም ሃገር ሊደርስ የሚችል መሆኑን አስጠንቅቀዋል።

ህንድ ባሁኑ ወቅት አስራ ስምንት ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ተያዦች ያልዋት ሲሆን ከህንድ የሚበልጥ ቁጥር ያላት ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ተጋላጮች መሆናቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የወረርሽኙ መረጃ ያመለክታል።

XS
SM
MD
LG