በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መቶ ቀናት


46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፕሬዚዳንታዊ ሥራቸውን የጀመሩበትን መቶኛ ቀን ምክንያት በማድረግ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ የመጀመሪያ ንግግራቸውን ያደርጋሉ።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ከሌሎች ሃገሮች ጋር አብሮ የመስራት ግቦቻቸውን እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚይዙትን የመሪነት ሚና ያስረዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ሲል የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ስለፕሬዚዳንቱ ንግግር በሰጡት ማብራሪያ ባይደን የውጭ ፖሊሲን በተመለከተ በሚያደርጉት ንግግር

"አሜሪካ በዓለም ላይ የነበራትን ሥፍራ እንደገና እንድትይዝ ማድረግ እንዲሁም የሀገራችን እሴቶች ምንነት ላይ ያተኩራሉ” ብለዋል።

ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ የውጭ ፖሊሲ ቅድሚያ ትኩረቶች ዙሪያም ማብራሪያ እንደሚሰጡ ቃል አቀባዩዋ ጠቅሰዋል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደሩን ከተረከቡ አንድ መቶ ቀናት ያሳለፉ ሲሆን በዚህ ታሪካዊ ወቅት ባሉት ፈተናዎች እና እድሎች ዙሪያ ያለዎትን ራዕይ በተመለከተ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር ያድርጉልን ብለው የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ እንደጋበዙዋቸው የዋይት ሃውሷ ቃል አቀባይ መግለፃቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ በዛሬ ማታው ንግግራቸው አብይ ትኩረት ሰጥተው የሚያብራሩበት የአገር ውስጥ ፖሊሲ ጉዳይ ለትምህርት እና ለህጻናት እንክብካቤ የሚመደብ መዋዕለ ነዋይ ያካተተው መርሃ ግብራቸው እንደሚሆን ጄን ሳኪ ገልጸዋል። ፀረ ኮቪድ-19 እና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የሚደረጉ ትግሎችን፣ ኢሚግሬሽን፣ የፖሊስ አሰራር ለውጦች እና የመሳሪያ ደህንነትም ላይ እንደሚያተኩሩ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG