በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


የኮቪድ-19 ክትባቶች
የኮቪድ-19 ክትባቶች

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል አሃዝ መሰረት በዓለም ዙሪያ አጠቃላዩ የቫይረሱ ተግላጮች ቁጥር 148,846,852 የገባ ሲሆን ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 3,138,755 ናቸው።

ዩናይትድ ስቴትስ በሁለቱም አሃዞች ከፍተኛውን እንደያዘች ናት።

ለቫይረሱ የተጋለጡት ቁጥር 32,179,505፣ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ብዛት ደግሞ 573,452 መግባቱን የሆፕኪንሱ መረጃ ያሳያል።

በሌላ ዜና ብሪታንያ ውስጥ የተካሄደ አንድ ጥናት የመጀመሪያ ወጤት እንደሚያሳየው በሁለት ጊዜ ከሚወሰዱት የኮቪድ-19 ክትባቶች የመጀመሪያውን የተከተበ ሰው ሁለተኛውን ከመከተቡ በፊት ለቫይረሱ ቢጋለጥ ቫይረሱን ወደሌላ ሰው የማስተላለፉ አደጋ በግማሽ ያህል ያነሰ ይሆናል።

ምርመሩን ያካሄዱት የኢንግላንድ የህዝብ ጤና ተቁዋም ተመራማሪዎች የፋይዘሩን ወይም የአስትራ ዜነኔካውን ክትባት የመጀመሪያውን ከተከተቡ ከሶስት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎችን የተከታተሉ ሲሆን አብረዋቸው ወደሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን የማጋባት ዕድላቸው ከሰላሳ ዘጠኝ እስከ አርባ ዘጠኝ ከመቶ በሚደርስ መጠን የቀነሰ እንደነበር ደርሰውበታል።

የብሪታንያ የጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ

“ይህ የሚያሳየን መከተቡ ከዚህ ወረርሽኝ የሚገላግለን፣ ከሁሉም ተመራጩ መንገድ ነው፤ አንድም ራሳችንን ከቫይረሱ እንጠብቃለን፣ ብንያዝ ደግሞ ባለማወቅ ወደሌላ የቤተሰብ አባል እንዳንስተላልፈው ይረዳናል” ብለዋል።

በሌላ ዜና የፋይዘር ኩባኒያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አልበርት ቡርላ በሰጡት ቃል ለኮቪድ-19 ህሙማን የምውል የሚዋጥ መድሃኒት፣ እአአ 2021 ማብቂያ በሚኖረው ጊዜ ውስጥ ዝግጁ እንደሚሆን ሲጠቅሱ የዩናይትድ ስቴትሱ የመድሃኒት ኩባኒያ ዋን ሥራ አስፈጻሚው ህመሙ እንደጀመረ የሚሰጠው ይህ መድሃኒት ህሙማኑ ሆስፒታል መግባት በሚያስፈልጋቸው ደረጃ እንዳይጸናባቸው የሚከላከል መሆኑን ነው የገለጹት።

XS
SM
MD
LG