በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ህንድ ውስጥ መናፈሻዎችና የመኪና ማቆሚያዎች በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች አስከሬኖች ማቃጠያ ስፍራ ሆኗል

ህንድ ውስጥ መናፈሻዎችና የመኪና ማቆሚያዎች በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች አስከሬኖች ማቃጠያ ስፍራ ሆኗል


ህንድ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች አስከሬኖች ሲቃጠል
ህንድ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች አስከሬኖች ሲቃጠል

ህንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አብዝቶ በበረታባት በህንድ በበሽታው ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ከ200,000 አለፈ።

ዛሬ ብቻ 3,290 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ የተመዘገበው ለቫይረሱ የተጋለጠው ህዝብ ቁጥርም 360,960 ሲሆን አጠቃላዩ ቁጥር ወደ 18ሚሊዮን ተቃርቧል። ሁኔታው ከዓቅም በላይ የሆነበት የሃገሪቱ የጤና ሥርዓት ሊፈራርስ ነው የሚል ስጋት አለ። ሆስፒታሎች በታካሚ ብዛት ከመጨናነቃቸው የተነሳ የባቡር ፉርጎዎችን ወድህሙማን ለይቶ ማቆያ እየቀየሩ ናቸው፥ የኦኮስጂን እጥረቱም ተባብሷል።

መናፈሻዎች እና የመኪና ማቆሚያዎች ሃያ አራት ሰዓት ያለማቋረጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አስከሬኖች ማቃጠያ ስፍራ ሆነዋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለህንድ እጅግ አጣዳፊ የሆኑ የህክምና እርዳታዎችን እየላከ ነው።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል አሃዝ መሰረት በዓለም ዙሪያ አጠቃላዩ የቫይረሱ ተግላጮች ቁጥር 148 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን የገባ ሲሆን ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 3ነጥብ አንድ ሚሊዮን አልፏል።

XS
SM
MD
LG