በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃኪሙ የኮቪድ-19 ማስታዎሻዎች


ዶ/ር ዳዊት በቀለ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሀኪም
ዶ/ር ዳዊት በቀለ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሀኪም

“ሃኪም ሆኖ መታመም በአንድ በኩል ትልቅ የህይወትም ልምድ ነው፤ ሌላው ባለፈበት ማለፍ። ድኖ ደግሞ በሽተኞችን መርዳት መቻል ለእኔ እንደ ትልቅ ዕድል ነው።” ዶ/ር ዳዊት በቀለ።

ኮቪድ-19 ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የከሰተውን ሁኔታ ወረርሽኙ ገና በጀመረበት፤ በተለይም በአውሮፓና በዩናይትድ ስቴትስ የሰውን ልጅ ህይወት ክፉኛ ማመሳቀል በያዘበት ሰሞን የአንድ ሃኪም ገጠመኞች ፈተና እና የህይወት መንገድ መለስ ብሎ የሚያስቃኝ ምልልስ ነው።

በጊዜው በዚያ የተለየ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ያነጋገርናቸውና ዛሬ መልሰን የጎበኘናቸው እንግዳችን የኮቪድ ታማሚዎች ከሚጎርፉባቸው የአውሮፓ ሆስፒታሎች በአንዱ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃኪም ናቸው።

ዶ/ር ዳዊት በቀለ ይባላሉ። በምሥራቃዊ ስዊድኗ የዑሜ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ያን የቀደመ ሁኔታ በዛሬ ውስጥ ወደሚያሳየን ወጋቸው እንውሰዳችሁ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ክፍል አንድ - የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃኪሙ የኮቪድ-19 ማስታዎሻዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:03 0:00


XS
SM
MD
LG