በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ መንግሥት


የፀጥታ ኃይል አባላት በቻድ ዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ
የፀጥታ ኃይል አባላት በቻድ ዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ

የቻድ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሀገሪቱ ወደ ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓት እንድትመለስ ለመጠየቅ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። የሰልፍ ጥሪ የቀረበው አዲሶቹ የቻድ ወታደራዊ መሪዎች አልበርት ፓሂሚ ፓዳኪን የጊዚያዊው መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ከሰየሙ በኋላ ነው። ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከሳምንት በፊት የሞቱት ከአማጽያን ጋር በተከፈተ ጥቃት መሆኑ ተዘግቧል።

ፓዳኪ በፕሬዚዳንት ደቢ ሥልጥን ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ወታደራዊ መማክርቱ ከአማጽያን ጋር በሚዋጋበት በአሁኑ ወቅት፣ ምርጫ ለማካሄድ የ18 ወራት የሽግግር ጊዜ ለማደረግ ቃል ገብቷል። እንደገና የተሰየሙት የቻድ የሽግግር ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓዳኪ፣ መረጋጋት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።

“ቻዳውያን እንደመሆናችን መጠን ተቃዋሚዎችም ሆኑ ብዙሃን፣ ሲቪል ማህበሰረስብም፣ ሴቶችም ሆኑ ወጣቶች የተደቀነብን ተግዳሮት የሰላም ጉዳይ ነው። እጅ ለእጅ ተያይዘን በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰርጽ ምን ማድረግ አለብን? በሀገራችን የጠብ-መንጃን ድምጽ እንዴት እናቁም?“ ብለዋል።

አንድ ተቃዋሚ መሪ ከአማጽያኑ ጋር ድርድር እንዲካሄድ ያቀረቡትን ጥሪ፣ የቻድ ወታደራዊ መማክርት አልተቀበለውም። ከዴቢ ሞታ ጋር በተያያዘ፣ ተጠያቂ የሆኑት ሁሉ፣ ታድነው መታሰር አለባቸው ይላል።

ዴቢ ባለፈው ሳምንት ሰኞ እለት፣ ከአማጽያን ጋር ይዋጉ የነበሩ ወታደሮችን ሲጎበኙ ከተገደሉ በኋላ ነው፣ ወታደራዊው ካውንስል ሥልጣን የያዘው።

ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ኩዴታ ወይም መፈንቅለ መንግሥት ብለዋታል። ሌሎች ደግሞ ወታደራዊው ሃይል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰየም መብት የለውም ብለዋል።

ወታደራዊው መማክርት የሚመራው፣ በሟቹ ፕሬዚዳንት ልጅ መሃማት ኢድሪስ ደቢ ነው። ጄኔራል ዴቢ ብሄራዊ ፕሬዚዳንት ተብለዋል። እናም የሀገሪቱን ምክር ቤት አፍርሰዋል።

የዩናይተድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ሚኒስትነት የተሰየሙት ሲቪል መሆናቸው፣ ሲቪል አስተዳደሩን ለመመለስ የሚያስችል፣ አዎንታዊ የመጀመርያ እርምጃ ነው ብሏል። ዋሽንግተን ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለች መሆኗን፣ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አክሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የቻድ መንግሥት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:28 0:00


XS
SM
MD
LG