በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥታቱ ድርጅት ሰለሰሜን ሸዋና ኦሮምያ ልዩ ዞን


በማኅበረሰቦች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት አማራ ክልል ውስጥ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም ውጥረት የነገሠበትና ያልተረጋጋ መሆኑን ከሰብዓዊ ረድዔት ባልደረቦቻችን አገኘነው ካሉት መረጃ መገንዘባቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ፋርሃን ሃቅ ትናንት ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ለመፈናቀሉ ምክንያት በሆኑትና ዝርፊያ፣ የንብረትና የመሠረተ ልማት ውድመት ባስከተሉት ግጭቶች በህይወትና በአካል ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን በውል እንደማይታወቅ አመልክተዋል።

መጋቢት 9/2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ አንድ ሰው መገደሉን ተከትሎ ግጭት መቀስቀሱን ቃል አቀባዩ ጠቅሰው ከሁለት ቀናት በኋላ በተፈፀሙ ጥቃቶች በሰሜን ሸዋ እና በኦሮምያ ልዩ ዞን አካባቢዎች ቢያንስ 60,000 የሚደርስ ቁጥር ያለው ሰው መፈናቀሉን፣ ተከትሎም ሚያዝያ 9/2013 ዓ.ም እንደገና በከተሞች መሃል እና በዋናዋና አውራ ጎዳናዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከቀደመውም የበለጠ ህዝብ መፈናቀሉንና መጠነ ሰፊ ጉዳት መድረሱን ፋርሃን ሃቅ አስረድተዋል።

በዚህ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የተፈናቀለውን ሰው ቁጥር ስፋት በውል ማረጋገጥ አለመቻላቸውን የሰብዓዊ ረድዔት አጋሮቻቸው እንደገለጹላቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ጠቅሰው፤ ይሁን እንጂ በሰሜን ሸዋና በኦሮምያ ልዩ ዞኖች ውስጥ የተፈናቃዩ ቁጥር በትንሹ 330,000 መሆኑን የክልሉን ባለሥልጣናት ጠቅሰው ተናግረዋል።

ሃቅ አስከትለውም ለተፈናቃዩ የሚያስፈልገው ረድዔትና የተደቀኑት አደጋዎች ሁኔታና መጠን ዳሰሳ የፀጥታው ሁኔታ እንደፈቀደ እንደሚከናወን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG