በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል


አዲስ አበባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ

በጤና ሚኒስቴር በእናቶችና ህፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት ለማኅበረሰባቸው አገልግሎት በመስጠት የቆዩት ወ/ሮ ነፃነት ብርሃኑ በኮቪድ-19 ተይዘው ተገቢው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እያሉ ሕይወታቸው ማለፉን በጤና ሚኒስቴር ፌስቡክ ገጽ የወጣው የሃዘን መግለጫ አመለከተ።

እንዲሁም በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ አገራቸውንና ህዝባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ማለፉንም የወጣው የሃዘን መግለጫ አመልክቷል።

ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ የ2012 ዓ/ም በጤና ዘርፍ በስራ አመራር ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ ስላበረከቱ ከጤና ሚኒስቴር እውቅና ያገኙ መሆናቸውን ጠቅሷል።

የጤና ሚኒስቴር ህዝበ ክርስትያኑ በዚህ በሰሞነ ህማማት በጸሎት እና በስግደት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳይዘናጋ ተግባራዊ እንዲያደርግ ተማጽኖውን አቅርቧል።

በተያያዘ ዜና አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በሃምሳ ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል። መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለሀገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።

በኢትዮጵያ ሬዲዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ የነበረ ሲሆን የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬዲዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ሥራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ያደረሰው መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት እንደነበረ ከአገር ውስጥ የዜና ማሰራጫ የወጣው ዜና አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG