በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ለምን ይመርጣሉ?"


ፎቶ ፋይል፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ መምህር ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ
ፎቶ ፋይል፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ መምህር ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ

የህዝብ አስተያየትና የባለሞያ ትንታኔ

ከሳምንታት በኋላ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከቀደሙት አምስት ምርጫዎች የተለየ እንደሚሆን የሚጠቁሙ በቂ ምልክቶች መኖራቸውን አንድ አንጋፋ የህገ መንግሥት ህግ ምሁር ተናግረዋል።

ምርጫ ቦርድን የመሳሰሉ የዴሞክራሲ ተቋማት እንደገና መደራጀት ደግሞ ከምልክቶቹ አንዱ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህገ መንግሥት ሕግ መምህር ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ ጠቁመዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የአዲስ አበባና የሌሎች ከተሞች ነዋሪዎችም ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ድምፅ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

ምርጫው ነፃና ጠንካራ ፉክክር የሚታይበት መሆኑን እንደሚጠራጠሩ የገለጹም አሉ።

የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ እና አሃዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በጋራ ያዘጋጁትና "ለምን ይመርጣሉ?" ሲሉ ዜጎችን የጠየቁበት፤ በባለሙያም ያስተነተኑበት የቴሌቭዥን ስቱዲዮ ውይይት ነው የዚህ ዘገባ መነሻ።

ውይይቱን የመሩት እስክንድር ፍሬው ከአሜሪካ ድምፅ እና ሊዲያ አበበ ከአሃዱ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ናቸው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

"ለምን ይመርጣሉ?"
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:24 0:00
ክፍል ሁለት - "ለምን ይመርጣሉ?"
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:58 0:00
ክፍል ሦስት - "ለምን ይመርጣሉ?"
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:27 0:00



XS
SM
MD
LG