በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮቪድ-19 የተጎዳችው ህንድ


ኮቪድ-19 በህንድ
ኮቪድ-19 በህንድ

ዛሬ ሰኞ 352 ሺሕ 991 ሰው በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበባት ህንድ በሁለተኛውና በከፍተኛ ሁኔታ በሚዛመተው ወረርሽኝ ከ300 ሺሕ በላይ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር በተከታታይ አምስት ቀናት ስለተመዘገበባት ከደቡብ እስያ ሃገሮች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳች ሃገር ሆናለች። በወረርሽኙ ከተያዙት ውስጥም 2ሺሕ812 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ዛሬ ሰኞ የተመዘገበ ሲሆን የቀብር ስፍራዎቹ ቀንና ማታ አስክሬን በማቃጠል ላይ በተጠመዱ ሰዎች ተሞልቷል።

የታማሚዎቹ ቁጥር ሆስፒታሎቹ አገልግሎት መስጠት ከሚችሉት በላይ በመሆኑ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ አዲስ ታማሚ መቀበል እና ማስተናገድ አይችሉል። በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ የኦክስጅን እጥረት በማጋጠሙ የሃገሪቱ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት አደጋ ላይ ወድቋል። በአሁን ሰዓት በመተንፈሻ መታገዝ የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች አየር እየሳቡ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

በኒው ደህሊ የተላለፈው እና ዛሬ ያበቃ የነበረው እቤት ውስጥ የመቀመጥ ውሳኔ ለአንድ ሳምንት ተራዝሟል።

የፖለቲካ ስብሰባዎችን ከልክለው በሚሊዮኖች የሚታደሙበትን የህንድ ሃይማኖታዊ በዓልን በመፍቀዳቸው ተቃውሞ የቀረበባቸው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናርዳር ሞዲ ትናንት በሬዲዮ ቀርበው “ኮቪድ ሕንድን እየነቀነቃት ነው” ብለዋል። ህንዳውያን በሙሉ ስለ ፀረ ኮቪድ-19 ክትባት በሚነገረው አሉባልታ ሳይዘጋጉ ክትባቱን እንዲከተቡ ተማፅኖ አቅርበዋል።

ሕንድ እስካሁን 138 ሚሊዮን ሰዎችን መከተብ ችላለች። ይሁንና ከ1.4 ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥሯ ውስጥ ከትባት ያገኘው 1.6 በመቶው ብቻ መሆኑን የጆንስ ሆፕኪንስ ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል መረጃ ያስረዳል።

በህንድ የተከሰተው ቀውስ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እጃቸው ለህንድ እንዲዘረጉና አስፈላጊ የሆኑ የሕክምና አቅርቦቶችንም ለመላክ እንዲጣደፉ እያስገደዳቸው ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፤ ዩናይትድ ስቴትስ ፀረ ኮቪድ ክትባትን ማበልፀግ የሚያስል ጥሬ እቃ ወደ ህንድ እንደምትልክ ትናንት እሁድ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጹሑፍ ቃል ገብተዋል። በተጨማሪም ቬንትሌተሮች፣ የመመርመሪያ መሳሪያ እና የመከላከያ ቁሳቁሶች እንደሚላክ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለስልጣናት ዩናይትድ ስቴትስ ካስቀመጠችው የአስትራዜኒካ ክትባት 20 ሚሊዮኑን ወደ ህንድ እንድትልከው እየጎተጎቱ ነው።

XS
SM
MD
LG