በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት መማረራቸውን የሃዋሳ ነዋሪዎች ገለጹ


ሀዋሳ
ሀዋሳ

ባልተገባ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት መማረራቸውን የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ገለጹ።

ጫፍ የወጣ ያሉትን የኑሮ ውድነት ያስከተለው ራስ ወዳድ ባለፀጎች የሚሰሩት ሸፍጥ እና የመንግሥት ተሿሚዎች ግድየለሽነት ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

ህዝቡን እያስጨነቀ ያለውን የኑሮ ውድነት የክልሉ መንግሥት ብቻውን ማስቆም እንደማይችል የተናገሩት የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ለዳሞ ተገቢ ያልሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ለመግታት ጥረት እየተደረገ መሆኑና በድጎማ መልክ ሊቀረቡ በሚችሉ ምርቶች ዙሪያ ከፌዴራል መንግስት ጋር በመካከር ላይ እንደሆነም ገልፀዋል።

ሀገሪቱ እንደአጠቃላይ የክልል ከተሞችም በተናጠል በእንደዚህ ዓይነት ቅጥ ያጣ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ውስጥ ሲዘፈቁ /ሲወድቁ የመውጫ መንገድ ምን ይሆን ብሎ ቪኦኤ የጠየቃቸው የሃዋሳ ዩኑቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ልዕቅ ዶ/ር ዴጌላ ኤርገና መልስ ሰጥተውናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት መማረራቸውን የሃዋሳ ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:50 0:00



XS
SM
MD
LG