በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነጆ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰው ተገደለ


ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ውስጥ ወርቅ በባህላዊ ዘዴ በሚለቀምበት ሥፍራ ላይ ባለፈው ሰኞ በተከፈተ ተኩስ ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፈ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ቦታው ላይ እንደነበሩ የገለፁና የዐይን እማኝ መሆናቸውን የገለፁ ግለሰብ በተኩሱ ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመው ገዳዮቹን ግን እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ግድያውን የፈፀሙት “ኦነግ ሸኔ” ብለው የጠሯቸው ታጣቂዎች እንደሆኑ አስተዳዳሪው ቢገልፁም "የኦሮሞ ነፃነት ጦር" ነን የሚሉት ታጣቂዎች የምዕራብ ዞን ቃል አቀባይ መሆናቸውን የገለፁት ቢሊሱማ ጉታ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ክሡን አስተባብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ነጆ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰው ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:39 0:00


XS
SM
MD
LG