በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በህንድ


ህንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ሥርጭት በከፋ ሁኔታ ማሻቀቡን ቀጥሏል። ባለፈው ሃያ አራት ሰዓት ውስጥ 332,730 አዲስ ተጋላጮች መገኘታቸውን አስታውቃለች። በቀደመው ቀን ከተመዘገበው ከፍተኛው የአንድ ቀን የተጠቂዎች አሃዝ የበለጠ መሆኑ ታውቋል።

በዋና ከተማዋ ኒው ዴልሂ አምስት ሆስፒታሎች ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚያስፈልግ ኦክሲጂን እንደጨረሱ ወይም እየጨረሱ እንደሆነም ተዘግቧል።

የኦክሲጂን እጥረቱ የከፋ ከመሆኑ የተነሳ የኒው ዴልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥት በየኢንዱስትሪው ያለውን አቅርቦት ወደሆስፒታሎች እንዲያዛውር ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በጆንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ጥንቅር መስረት የህንድ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ቁጥር ወደአስራ ስድስት ሚሊዮን እያተቃረበ ነው። ከዓለም ትልቁን የቫይረሱን ተጋላጮች በያዘችው በዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ አሃዙ ወደሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ተቃርቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሦስት ወራት በኋላ የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ውድድር የሚከፈትባት ጃፓን በወረርሺኙ እየተባባሰ መምጣት የተነሳ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልታውጅ መሆኑ ተዘግቧል። ዛሬ የጸረ ኮቪድ ሚኒስትሩ በሰጡት ቃል ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑ በጣም እያተሰማን ነው ብለዋል። በጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ መሰረት ጃፓን ውስጥ ያሉት የቫይረሱ ተጋላጮች ከግማሽ ሚሊዮን አልፏል።

XS
SM
MD
LG