በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ክትባትን ለራሳቸው ብቻ የሚሰበስቡ ሀገሮችን ነቀፈ


የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለምን የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት ለራሳቸው ብቻ የሚሰበስቡ ሃገሮች አጥብቀው ነቀፉ።

ዶ/ር ቴድሮስ በቅርቡ በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ባወጡት ጽሁፋቸው ክትባቱን ማግኘት ለሚቸግራቸው ሃገሮች ለማቅረብ በዓለም የጤና ድርጅት አሰባሳቢነት በተቋቋመው በኮቫክስ አማካይነት የሚደረገውን ጥረት

“ክትባት ለራስ ሃገር ብቻ መሰብሰብ" ሲሉ በገለጹት አድራጎት ጥረቱ እየተዳከመ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ጥቂት ከበርቴ ሃገሮች የሚመረቱ ክትባቶችን የበለጠ ዋጋ ለሚከፍላቸው ከሚሸጡ ኩባኒያዎች ላይ ተቀራምተው በመግዛት የሚያግበሰብሱበት ሌሎች ትርፍራፊው የሚቃርሙበት ሁኔታ እየታየ ነው ብለዋል።

አያያዘውም ወረርሽኙን ለመዋጋት መፍትሄው ቀላል ነው፣ ያም ማካፈል ወይስ አለማካፈል ከሁለት አንዱን የመምረጥ ጉዳይ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አስከትለውም በዚያ ደግሞ የሚፈተነው ሳይንስ ወይም የኢኮኖሚ እና የኢንዱስትሪ አቅም ሳይሆን የሚፈተነው ማንነታችን ነው" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG