በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ቁጥር ከ250 ሺሕ በልጧል ተባለ


በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን መፈናቀል ያወገዘ ሰልፍ በደሴ ከተማ ተካሄደ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ላይ በደረሰው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ከሩብ ሚሊዮን እንደሚልቁ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታወቀ። ከጥቃት አምልጠው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እና የአማራ ክልል መንግሥት ጥቃቱ በከባድ የጦር መሳሪያ የታገዘ እንደሆነ ገልፀዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በበኩሉ “ኦነግ ሸኔ የለበትም” ብሏል።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ተፈናቃዮቹን መልሶ ለማቋቋም በመንግሥት አቅም ከባድ መሆኑን በመግለፀም የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤቱ የአጋር አካላትን ትብብር ጠይቋል።

በተያያዘም በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግድያና መፈናቀል ያወገዘ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በደሴ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ሰልፈኞቹ “ፍትህ ለአማራ ሕዝብ” ሲሉ ተደምጠዋል።

የፌዴራል መከላከያ ሚኒስትር የአካባቢውን ጸጥታ ለማረጋገጥ ሰሜን ሸዋን ጨምሮ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና ደቡብ ወሎ ዞኖች ላይ ኮማንድ ፖስት አቋቁሟል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ቁጥር ከ250 ሺሕ በልጧል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:17 0:00


XS
SM
MD
LG