በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሚኒሶታ ክ/ግዛት ውስጥ የአንድ ግለሰብ ግድያን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ


ዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት አንድ ግለሰብ በፖሊስ ጥይት መገደሉን ተከትሎ ሰዎች በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት አንድ ግለሰብ በፖሊስ ጥይት መገደሉን ተከትሎ ሰዎች በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት አንድ ግለሰብ በፖሊስ ጥይት መገደሉን ተከትሎ ትናንት ሰኞ ማታ በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ሚኒያፖሊስ ከተማ ዳርቻ የሚገኘው የብሩክልን ሴንተር አካባቢ የሌሊት የሰዓት እላፊ የታወጀ ሲሆን ፖሊሶች ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝና ማስደንገጫ ፈንጂ ወርውረውባቸዋል።

ዳንቴ ራይት የተባለው የሃያ ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊስ ጥይት የተገደለው የትራፊክ መብራት ላይ ሲሆን የብሩክልን ሴንተር ፖሊስ አዛዥ ቲም ጋነን ፖሊሷ ቴዘር የሚባለውን የማይገድል ነገር ግን የሚያዘውን ሰው በኤሊክትሪክ ንዝረት የሚያልፈሰፍስ መሳሪያ የተኮሰችበት መስሏት ጥይቱን ሳይተኩስበት አልቀረችም ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

የሚኒሶታ ክፍለ ግዛት ጉዳዩ ላይ ምርመራ የከፈተ ሲሆን ፖሊሷ በአስተዳደራዊ ትዕዛዝ ታግዳለች። የከተማዋ ከንቲባ ፖሊሱዋ መታገድ ሳይሆን መባረር አለባት ብለዋል።

የሰው ህይወት የሚያጠፋ ስህተት መስራት አንችልም፤ በዚህ ጉዳይ ፍትህ እንዲሰጥ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉም ከንቲባው አክለዋል።

የሙሟ ወንድም በትናንቱ የሻማ ማብራት የተቃውሞ ትዕይንት ላይ ባደረገው ንግግር "ፖሊሷ እንደምን ጥይትን ከቴዘር ከንዝረት ለቃቂ አልቻለችም? ፕላስቲክና ብረት አንድ አይደለም፤ ሁላችንም እናውቃለን ብሏል።

ጉዳዩን አመልክተው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ቃል የሆነውን ነገር የሚካሄደውም ምርመራ ይለየዋል ብለዋል። ዕሁድ ማታ ከተካሄደው ተቃውሞ በኋላ የተፈጸመው ዝርፊያ ግን በምንም ምክንያት ሊፈጸም የማይገባ ነው ብለዋል።

ባይደን ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ሰላም እና እርጋታ እንዲሰፍን እማጸናለሁ። የዳንቴ እናት ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያደርጉትን ጥሪ ማስማት አለብን። የሟቹ እናት ለተቃውሞ ሰልፈኞች “ሰላማዊ ሆናችሁ ትኩረታችሁን የሞተው ልጄ ላይ አድርጉ” ሲሉ ተማጽነዋል።

XS
SM
MD
LG