በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ፍትሃዊነት የጎደለው የኮቪድ ክትባት ሥርጭት በአፍሪካ"- የዓለም ጤና ድርጅት


በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ማሺድሶ ሞኤቲ
በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ማሺድሶ ሞኤቲ

የዓለም ጤና ድርጅት፣ ፍትሃዊነት የጎደለው የኮቪድ-19 ክትባት ሥርጭት፣ በአብዛኛው ጎልቶ የሚታየው 600 ሚሊዮን ከሚሆኑ ክትባቶች ውስጥ የተወሰነው ክፍል ብቻ በተሰራጨበት አፍሪካ ውስጥ መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡

በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ማሺድሶ ሞኤቲ፣ ኮንጎ ብራዛቪል ከሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዋና ጽ/ቤት፣ በበይነመረብ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው ወረረሽኙን በመመከት ውስጥ ክትባት የህይወት አድን መሳሪያ መሆኑን ተናግረው ይሁን እንጂ የሥርጭቱ ኢፍትሃዊነት ግን በቢሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያንን ወረርሽኙ ለመግታት ከሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ ነጥሎ አስቀርቶታል ብለዋል፡፡

ሞኤቴ ጨምረው እንደተናገሩ እንደ ጋና ሩዋንዳ እና አንጎላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀላል የማይባል የክትባት ስርጭት በተሳካ መንገድ ማከናወን የቻሉ ሲሆን፣ ለዚህም የረዳቸው ጥሩ የሠራተኞች ሥልጠና መከናወኑ ቅድም ዝግጅት መደረጉና ማኅበረሰቡንና ቡድኖችን ቀድሞ መመዝገብ በመቻላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ኃላፊዋ አስር የአፍሪካ አገሮች በአህጉሪቱ ከተሰራጨው ክትባት ውስጥ ከሁለት ሦስተኛ እጅ በላይ የሚሆነውን መጠቀማቸውን ተናግረዋል፡፡ እንደ ቤኒን፣ ኮሞሮስ፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን እና ደቡብ ሱዳን በገንዘብ ድጋፍ፣ እቅድና የሰው ኃይል እጥረት የተነሳ ክትባቱ የዘገየባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ኃላፊ እንደተናገሩት የዓለም ጤና ድርጅት ከሚያስተባብረውና በጄኔቭ ከሚገኘው ከዓለም አቀፉ የክትባት ስርጭት ኮቫክስ፣ በቅርቡ ለጊኒ ቢሳዎ፣ ሞሪታኒያ፣ ኒጀር፣ ካሜሩን እና ኮሞሮስ የክትባት ሥርጭት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሞኤቲ፣ የመድሃኒት አምራች ድርጅቶቾ የኮቪድ 19 ክትባትን በርከት አድርገው እንዲያመርቱ ጠይቀዋል፡፡ የበለጸጉ ሃገሮችም ፈጠን ብለው “የገቡትን ቃል በተግባር በመፈጸም ከተትረፈረው

XS
SM
MD
LG