በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒው ዚላንድ የጉዞ ዕገዳ


ኒው ዚላንድ ከፊታችን ዕሁድ ጀምሬ ከህንድ የሚመጣ ተጓዥ አላስገባም ብላለች። ምክንያቱ ደግሞ ከወደዚያ የሚመጡ መንገደኞች ላይ በብዛት ኮሮናቫይረስ እየተገኘ በመሆኑ ነው ብላለች።

በቅርቡ ለይቶ ማቆያ ካስገባቻቸው ሃያ ሦስት አዲስ የቫይረሱ ተያዦች መካከል አስራ ሰባቱ ከህንድ የገቡ መሆናቸውን ኒው ዚላንድ አስታውቃለች።

ከፊታችን ዕሁድ እስከ ያዝነው የአውሮፖ ሚያዝያ 28 የሚጸናው የጉዞ ዕገዳ ከህንድ የሚገቡ የኒው ዚላንድ ዜጎችንም ጭምር የሚመለከት መሆኑንም አስታውቃለች።

በአሁኑ ወቅት ህንድ የኮሮናቫይረስ ተያዦቿ ቁጥር ወደ አስራ ሦስት ሚሊዮን ተቃርቧል። ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከብራዚል ቀጥሎ ከፍተኛው አሃዝ ሲሆን ትናንት ብቻ 126789 ተያዦች ተመዝግቧል።

ቫይረሱ ለሁለተኛ ዙር በፍጥነት መዛመት በያዘበት በዚህ ወቅት ህንድ 1 ነጥብ ሦስት ቢሊዮኑን ህዝቧን የበሽታውን መከላከያ ለመከተብ እየተጣደፈች ትገኛለች።

XS
SM
MD
LG