በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልውጡ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዩናይትድ ስቴትስ


የሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋሌንስኪ
የሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋሌንስኪ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በዋናነት እየተዛመተ ያለው ባለፈው ታህሳስ ወር ብሪታንያ ላይ የተቀሰቀሰው ‘B.1.1.7’ ተብሎ የሚታወቀው ልውጡ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓይነት መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሲዲሲ/ አስታወቀ።

ሲዲሲ ባለፈው ጥር ወር ልውጡ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የቀድመው መጋቢት ወር ላይ ስንደርስ በሀገሪቱ የሚዛመተው ዋናው ዓይነት እንደሚሆን ተንብዮ እንደነበር ይታወሳል።

የሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋሌንስኪ ትናንት ረቡዕ በዋይት ሃውስ ባደረጉት ገለጻ

"አሁንም ከቫይረሱ አልተላቀቅንም፣ ሰዎች እየተያዙ ለጉዳት እየተዳረጉ ነው ስለዚህም ነቅተን መከላከል አለብን" ብለዋል።

ባሁኑ ጊዜ በዩናያትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከሠላሳ ሚሊዮን አልፏል፥ በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥርም ከ559116 በላይ ማሻቀቡን የጃንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ መረጃ ማዕከል አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG