በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ስላው ሰብዓዊ ሁኔታ - ተመድ


map of Ethiopia
map of Ethiopia

በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ከሰብዓዊ እርዳታ ባልደረቦቻችን እየሰማን ነን ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች ተናገሩ።

በክልሉ በሰብዓዊ ረድዔት ተደራሽነት ረገድ ትልቅ መሻሻል እንዳለ የተናገሩት ዱጃሪች ሆኖም በሰሜን ምዕራብ፣ በማዕከላዊ፣ በምስራቃዊ እና በደቡብ ምስራቃዊው እና በደቡባዊው ዞኖች አሁንም ግጭት መኖሩን ሪፖርቶች ደርሰውናል ብለዋል።

ስቴፋን ዱያሪች ለጋዜጦች ባደረጉት ዕለታዊ ገለፃ አንዳንዶቹ የሰብዓዊ ረድዔት አጋሮቻችን በክልሉ በደቡባዊ እና ደቡብ ምስራቃዊ ዞኖች ግጀት እና ሳምረ ከተሞች ለመግባት እንደቻሉ ገልጸው ሆኖም አብዛኞቹ የከተሞቹ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል ብለውናል ሲሉ ዱያሪች ጠቅሰዋል። አላማጣን፣ መቀሌን፣ አዲግራት እና ሽሬን የሚያገናኘው መስመር አሁንም በከፊል ክፍት መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ባለፉት አምስት ወራት ወደ 2ነጥብ 5ሚሊዮን የሚሆኑ የትግራይ ገጠራማ አካባቢዎች ነዋሪዎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዳላገኙ የረድዔት ባልደረቦቻችን ገልጸውልናል ብለዋል።

በግጭቱ ምክንያት በብዙ ሺህዎች የተቆጠሩ ሰዎች ከገጠሩ መቀሌን እና ሽረን ጨምሮ ወደከተሞች እየተሰደዱ መሆናቸውንም ሰምተናል ያሉት ዱያሪች በቅርብ ጊዜ በወጣ የግምገማ ሪፖርት መሰረት ሽሬ ከተማ ያሉት ተፈናቃዮች ቁጥር 450,000 ሊደርስ ይችላል ሲሉ አክለዋል።

የሰብዓዊ ረድዔት አጋሮቻችን በክልሉ ነፍስ አድን ርዳታ ለሚያስፈልገው ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በቂ እርዳታ ለማድረስ ካለባቸው የአቅም እንዲሁም የገንዘብ እና የአቅርቦት ችግር ጋር እየታገሉ ጥረት እያደረጉ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG