በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ


በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በሀርጌሳ ፖሊስ መታሰራቸውን በሶማሊላንድ የሚኖሩ ስደተኞች ተናገሩ።

በሶማሊላንድ ስደት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሀርጌሳ ፖሊስ በቁጥጥር እያዋላቸው መሆኑን ገልጹ። በሀርጌሳ የስደተኞች ተወካይ አቶ ኢማና ኃይሉ፣ ፖሊስ የተገን ጠያቂ ወረቀት ያላቸውን ስደተኞች አላግባባ እያሰረ መሆኑን፣ ገሚሳቸውን ደግሞ አለፍቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ እየመለሳቸዉ ነው ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስደተኞች ጉዳይ ከሶማሊያና ከሶማሊላንድ አስተዳደሮች ጋር ስለችግሩ እየተወያየ መሆኑን ለቪኦኤ ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በሶማሊላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:54 0:00


XS
SM
MD
LG