በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂ ሰባት ስለኢትዮጵያ


የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ተግባራት አገልግሎት
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ተግባራት አገልግሎት

የሰባቱ የዓለም ባለጸጋ ሃገሮች ቡድን /ጂ ሰባት/ ሃገሮች የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ የትግራይ ክልል እንዲወጡ አሳሰቡ።

ዛሬ በርሊን ላይ ዓመታዊ ጉባኤያቸውን የከፈቱት የሰባቱ የ ጂ ሰባት አባል ሃገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባወጡት መግለጫ የኤርትራ ወታደሮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ፥ ለማረጋገጥ በሚቻልበት መንገድ በአስቸኳይ ከትግራይ እንዲወጡ ሲሉ ጠይቀዋል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኤርትራ ወታደሮች በቅርቡ እንደሚወጡ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የጂ ሰባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በመግለጫቸው በክልሉ ሁሉም ወገኖች ከፍተኛውን መቆጠብ እንዲያሳዩ የሲቪሎችን ደህንነት እንዲጠብቁ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ደንቦችን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን እንዲያከብሩ እንጠይቃለን ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ፣ የብሪታኒያ፣ የካናዳ፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የጣሊያን እና የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ባወጡት መግለጫ "ሁከቶቹ እንዲያከትሙ እንዲሁም የትግራይን ህዝብ ጨምሮ በሁሉም ኢትዮጵያውን ዘንድ ተቀባይነት ያለው ግልጽ እና አሳታፊ የፖለቲካ ሂደት እንዲመሰረት እንጠይቃለን ያም ወደተዓማኒ ምርጫዎች እና ሰፋ ወዳለ የብሄራዊ እርቅ ሂደት ማምራት ይኖርበታል ብለዋል።

በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሰብዓዊ መብት እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ህግ ጥሰቶች በቅርቡ የወጡ ሪፖርቶች በጥልቅ አሳስበውናል ሲሉም የጂ ሰባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ አመልክተዋል።

የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ክልል መግባታቸውን ዲፕሎማቶች፣ የረድዔት ሰራተኞች፥ የክልሉ ነዋሪዎች እና እንዳንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቢናገሩም እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሁለቱም ሃገሮች ሲያስተባብሉ መቆየታቸው ይታወሳል።

በትግራይ ክልሉ ግጭት የብዙ ሺህዎች ህይወት መጥፋቱን ብዙ መቶ ሺህዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ ነዋሪዎች የምግብ፥ የውሃ እና የመድሃኒት ችግር ላይ ያሉ መሆኑን ዜናው ጨምሮ አውስቷል።

XS
SM
MD
LG