በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተፈናቃዮች ደቡብ ወሎ ውስጥ ተጠልለዋል


ከኦሮምያና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ
ከኦሮምያና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ

ኑሯቸውን በኦሮምያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አድርገው የነበሩ ከስምንት መቶ በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች በክልሎቹ በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ወሎ ዞን መግባታቸውን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ይህም ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ተፈናቀለው ወደ ዞኑ የገቡትን ሰዎች ቁጥር ከ10 ሽህ በላይ እንዲያሻቅብ አድርጎታል ነው የሚለው ጽ/ቤቱ፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መሳይ ማሩ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳስታወቁት በኦሮምያ ክልል ወለጋና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት 827 የአማራ ብሔር ተወላጆች ቤት ንብረታቸውን ጠለው ባለፉት ሦስት ቀናት ወደ ደቡብ ወሎ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ተፈናቃዮች ደቡብ ወሎ ውስጥ ተጠልለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:10 0:00


XS
SM
MD
LG