በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሮትና የልምጭ አካሄድ በመተከል


ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ
ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል አቅራቢያ ትናንት እረፋዱ ላይ የታጠቁ ሃይሎች በአውቶብስ ላይ በከፈቱት ተኩስ የ7 ንፁሀን ዜጎች ህይወት አልፏል።

የፀጥታ ሀይሉ በአካባቢው ፈጥኖ በመድረሱ 10 ታጣቂዎችን መደምሰሱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ጄኔራሉ እንዳሉት ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ፀጥታ ለመመለስ ያቀደው ታጣቂዎች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ በማድረግና እምቢ ባሉት ላይም እርምጃ በመውሰድ ነው። እስካሁንም 3500 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጥተው የታህድሶ ስልጠና እየወሰዱ ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የካሮትና የልምጭ አካሄድ በመተከል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00


XS
SM
MD
LG