በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ ክትባት በአውሮፖ ሃገሮች


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓ ዳይሬክተር ዶ/ር ሃንስ ክሉግ
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓ ዳይሬክተር ዶ/ር ሃንስ ክሉግ

የአውሮፓ ሃገሮች የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ በተገቢው መንገድ የተፋጠነ አለመሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አሳሰበ።

በአህጉሪቱ ሃገሮች ከአምስት ሳምንታት በፊት 1ሚሊዮን ገደማ የነበረው የአዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ቁጥር በአሁኑ ወቅት አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን መግባቱን ድርጅቱ አመልክቷል። የተከተቡት ሰዎች ቁጥር ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት አራት ከመቶ ብቻ መሆኑንም ጠቅሷል። በዚሁ ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው ወደሃያ አራት ሺህ ገደማ ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ መሞታቸውን ነው ድርጅቱ አክሎ ያመለከተው።

የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓ ዳይሬክተር ዶ/ር ሃንስ ክሉግ የአህጉሪቱ መሪዎች ክትባቱን አፋጥነው እንዲያዳርሱ አሳስበዋል።

የድርጅቱ የአውሮፓ አጣዳፊ ሁኔታዎ ድሬክተርዋ ዶ/ር ዶሪት ኒትዛን በበኩላቸው ከብሪታንያ የተቀሰቀሰው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በቀላሉ የሚዛመት እንደመሆኑ ተጨማሪ ጠንካራ የመቆጣጠሪያ ርምጃዎች መውሰድ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የፈርንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዌል ማክሮ በሃገራቸው ለሦስተኛ ጊዜ በብዛት እየተዛመተ ያለውን ቫይረስ ለመቆጣጠር ለሦስተኛ ጊዜ አገር አቀፍ የእንቅስቃሴ ክልከላ ትዕዛዞች አውጥተዋል። ትምህርት ቤቶእችች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለሦስት ሳምንት ይዘጋሉ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG