በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍልሰተኞች ጀልባ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት አለፈ


ብዛት ያላቸው ፍልሰተኞችን ጭኖ ወደአውሮፓ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሊቢያ ባህር ጠረፍ ላይ ተገልብጦ ሁለት ሴቶች እና ሦስት ህጻናት ሰጥመው ህይወታቸውን ማጣታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በማዕከላዊ ሜዴታራኒያን ባህር መስመር ከደረሰው አደጋ አንድ የአሳ አጥማጅ መርከብ እና የሊቢያ የጠረፍ ጥበቃ ሃይሎች ደርሰው ወደ ሰባ ሰባት የሚሆኑትን ለማውጣት መቻላቸው ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG