አምቦ —
በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት ጥቃት አድርሰው ሲቪሎችን መግደላቸው ታውቋል።
በጥቃቱ 28 ሰዎች መገደላቸውንና 14 መቁሰላቸውን ለቪኦኤ የገለፁት የዞኑ ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አደጋውን የጣሉት መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው ታጣቂዎች እንደሆኑ በመግለፅ ከስሰዋል።
ጥቃቱን ከፈፀሙት ታጣቂዎች መካከል ሦስቱ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ "በወረዳው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተግደለዋል" ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡