በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውስትራሊያ በትግራይ ክልል ጉዳይ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብትች ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ግጭቶች በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድራጎቶችን በጋራ የሚያጣሩ መሆኑ አስደስቶናል ስትል አውስትራሊያ አስታወቀች።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሴቶች ሚኒስትር ማሪስ ፔይን ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን የድንበር ግዛቶች ለቅቀው እንደሚወጡ ማስታወቃቸው ጠቃሚ ርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙትን በሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠያቂ እንዲያደርግ መወትወታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

አስከትለውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ትግራይ ውስጥ በተቀነባበረ መንገድ የደረሱ ወሲባዊ እና ሌሎችም ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥቃቶች መድረሳቸውን የሚያመለክቱት ሪፖርቶች አብዝተው ያሳሰቡን መሆኑን እናስታውቃለን ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

በዚሁ ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት በጋራ ያወጡትን መግለጫ አጥብቀን እንደግፋለን ብለዋል። ሃገራቸው በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች መርጃ የሚውል ሦስት ሚሊዮን ዶላር ለዓለም የምግብ ፕሮግራም እንደምትለግስ ሚንስትሯ አክለው አስታውቀዋል። ክልሉ በአስቸኳይ ለሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ተደራሽነት እንዲከፈት እየቀረበ ያለውን ጥሪ እኛም አብረን እናሰማለን ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ችግር ላይ ላሉ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት አድርገናል ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG