ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትሱን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን መልዕክት ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሴናተር ክሪስ ኩንስ ስለጉብኝታቸውና ስለ አነጋገሯቸው ባለሥልጣናት በአለፈው ሳምንት አጋማሽ በዋይት ሃውስ የደህንነት ጉዳዮች ምክር ቤት ማብራርያ ከጋዜጠኞች እና ከሴናተሮች ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል።
ሴናተር ኩንስ በሁለት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ሁለት ጊዜ ተገናኝተው በአጠቃላይ ለአምስት ሰዓታት ያህል መወያየታቸውን አመልክተዋል። ትግራይ ውስጥ ሰብዓዊ ዕርዳታ ያለ አንዳች ገደብ መድረስ እንዲችል እንደሚያደርጉ እና በሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በሲቪሎች ላይ ተፈጽመዋል በሚባሉ ጥቃቶች ተጠያቂዎች ሁሉ ሕግ ፊት እንደሚቀርቡ ጠ/ሚኒስትሩ እንደነገሯቸውና ለልዑካኑ የሰጡት ጊዜ እንዲሁም ላደረሱላቸው የፕሬዚዳንት ባይደን መልዕክት የነበራቸውን አቀባበል ንቃት እንደሚያደንቁ ሴናተር ኩንስ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ጠ/ሚሩ ቀደም ሲልም ቃል ገብተው ያልፈጸሟቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሴናተር ኩንስ በማብራሪያቸው ጠቁመዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡