መቀሌ —
በአክሱም ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመውን ግድያ ለመዘከር ከቤት ያለመውጣት ተቃውሞ በትናንትናው ዕለት መካሄዱ ተዘገበ።
በክልሉ ተፈፅመዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለማጣራት የተያዘውን ዕቅድንም ኮሚሽኑ ገለልተኛ አይደለም በሚል መቃወማቸውን፣ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉም የምሰራቸው ሥራዎች ገለልተኛ እና ተዓማኒ መሆናቸውን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የማካሂዳቸው ምርመራዎች ያለውን ጠቅሶ ዘጋቢያችን አድርሶናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡