በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚሩ በሰሜን ሸዋ እና በከሚሴ አካባቢ ያለመረጋጋት ጉዳይ ላይ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ፖለቲከኞች የመጡበትን አካባቢ ችግር ብቻ በማጉላት ለዘመናት የዘለቀን የህዝቦች አንድነት አደጋ ላይ እንዳይጥሉ በሰከነ መንፈስ ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡

ዛሬ ከተወካዮች ም/ቤት አበላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከሚሴና በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ለተከሰተው ግጭት ምክንያቱ ፖለቲከኞች ናቸው ብለዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ሲካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትኩረት ከሰጡባቸው ነጥቦች አንዱ በቅርቡ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ አካባቢ ተቀስቅሶ እስከ ከሚሴ ድረስ በተስፋፋው ግጭት ዙሪያ ነበር፡፡

ለሰዎች ሞት፣ ለንብረት ውድመት፣ ለአካል ጉዳትና መፈናቀል ምክንያት የሆነውን በከባድ ጦር መሳረያ የታገዘ ግጭት እንዲባባስ ያደረጉት ፖለቲከኞች እንጂ ህዝቡ ለዘመናት በአብሮነት የቆየ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ጠ/ሚሩ በሰሜን ሸዋ እና በከሚሴ አካባቢ ያለመረጋጋት ጉዳይ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00


XS
SM
MD
LG