በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሊንከን አጋርነትን ማጠናከር ላይ የታለመው የአውሮፓ ጉብኝት


ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ ዋና ጸኃፊ ስቶልትንበርግ
ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ ዋና ጸኃፊ ስቶልትንበርግ

ዩናይትድ ስቴትስ ያሏትን አጋርነቶች ከኔቶ ሸሪኮችዋ ጋር ላላት አጋርነት ዋናውን ቅድሚያ ሰጥታ መልሳ ለመገንባት የምትፈልግ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ተናገሩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ብረሰልስ ላይ ከሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ ዋና ጸኃፊ ስቶልትንበርግ ጋር ሆነው ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የባይደን አስተዳደር ለኔቶ አጋርነቱ ባለው ቁርጠኝነት በጽናት ይቆማል ብለዋል። ከዚያም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና የኔቶ ዋና ጸሃፊው ወደሚኒስትሮች ጉባዔ ከመግባታቸው አስቀድመው ውይይት አድርገዋል።

ስቶልትንበርግ በሰጡት ቃል የአዲሱን የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር አቀራረብ በደስታ እንደተቀበሉት ገልጸው ለአትላንቲክ ተሻጋሪ ግንኙነቶች መጀመር ልዩ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

በሁለት ቀናቱ የብረሰልሱ ስብሰባ ላይ አንደኛው ዋና ትኩረት የሚሆነው የኔቶ የአፍጋኒስታን ተልዕኮ መሆኑ ታውቋል። በቀድሞው ፕሬዚደዳት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር እና በአፍጋኒስታን ታሊባን መካከል ባለፈው ዓመት በተደረሰ የሰላም ስምምነት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በሙሉ የሚወጡበት የአውሮፓ አቆጣጠር ግንቦት አንድ የጊዜ ገደብ እየተቃረበ ነው።

XS
SM
MD
LG