በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአስትራዜኒካ ክትባት የተደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ይደረጋል


የአውሮፓ ህብረት የመድሃኒት ቁጥጥር ተቋም መርማሪዎች በአስትራዜኒካ ክትባት ደህንነት ጉዳይ ሲያካሂዱ የቆዩትን ምርመራ ውጤት ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተገለጸ።

ክትባቱን በወሰዱት ሰዎች ላይ የተፈጠረው የደም መርጋት ከክትባቱ ጋር ግንኙነት ይኖረው፣ አይኖረው እንደሆነ ሲመረምሩ ቆይተዋል።

የአውሮፓ የመድሃኒት ቁጥጥር ተቋሙ በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገሮች የአስትራ ዜኔካ ኩባኒያውን ክትባት ከወሰዱት አምስት ሚሊዮን ሰዎች መካከል በሠላሳ ሰዎች ላይ ተከስቷል የተባለውን፣ ከደም መርጋት ጋር የተያያዘ ችግር ክትትል ሲያደርግበት ከርሟል።

አንዱ ተመራማሪዎቹ የተከታተሉት ጉዳይ፣ ክትባቱን በወሰዱት ሰዎች ላይ የታየው የደም መርጋት፣ ከአጠቃላይ ህዝቡ ማናቸውም ሰው ላይ ከደረሱት ተመሳሳይ ችግሮች በይበልጥ ደጋግሞ ተከስቷል ወይ? የሚለውን ጥያቄ በጥናታቸው አካተዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ አሁን ያሉ መረጃዎችን ተመርኩዞ የራሱን ጥናት እንደሚያካሂድ ትናንት አስታውቋል። ለጊዜው ግን ክትባቱ ሊያስከትል ከሚችለው የጎንዮሽ አደጋ የሚሰጠው ጠቀሜታ እንደሚበልጥ እናምናለን ብሏል።

ህንድ ክትባቱን ለህዝቧ መስጠቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG