በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞደርና ክትባት ሙከራ ለህፃናት


የዩናይትድ ስቴትሱ የመድሃኒት ኩባኒያ ሞደርና ክትባቱ ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ለሆኑ ወጣቶችም ጭምር መሰጠት ይገባው እንደሆነ ለመፈተሽ ልጆችንና ታዳጊዎችን ያሳተፈ ሙከራ ጀምሯል።

ሞደርና በጀመረው በዚህ ጥናቱ ዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ የሚኖሩ ከ6750 በላይ የሆኑ ከስድስት ወር ህጻን እስከ አስራ ሁለት ዓመት የሆኑ ልጆችን ለሙከራ እየከተበ መሆኑ ታውቋል።

በሁለት ዙር የሚሰጠው ይህ ክትባት በሙከራው ለሚሳተፉት ልጆች የሚሰጠው በሃያ ስምንት ቀናት ተራርቆ ሲሆን ለዝህ ምክንያቱ ተመራማሪዎቹ ክትባቱ የጎንዮሽ ጠንቅ የሚያመጣ ከሆነ ለማወቅ እና ምን ያህል በልጆች ላይ ቫይረሱን ለመከላከል ውጤታማ እንደሚሆን ለማየት ጊዜ እንዲያገኙ ተብሎ መሆኑ ተገልጿል።

የሞደርና ኩባኒያው ጥናት የሚካሄደው በክትባት ስራው ከረዳው ከዩናይትድ ስቴትስ የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ጋር በትብብር መሆኑም ታውቋል።

ሞደርና ከዚህኛው ሙከራው በፊትም ባለፈው ታህሳስ ወር ከአስራ ሁለት ዐመት እስከ አስራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ውስጥ ባሉ ሶስት ሺህ ታዳጊዎችና ወጣቶች ላይ የክትባቱን የጤና አደጋ ማስከተል አለማስከተል እና ውጤታማነቱን ለመፈተሽ የታለመ ሙከራ ሲያካሂድ ቆይቷል።

XS
SM
MD
LG