በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦፌኮ ቅሬታ እና ምላሹ


በምዕራብ ኦሮምያ አንዳንድ ዞኖች የሚገኙ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ፓርቲ ተወካዮች ፅህፈት ቤቶቻቸው “ሁሉም ማለት በሚያስችል ደረጃ” መዘጋታቸውን ገልፀዋል።

"በርካታ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎችና የአመራር አባላት በመታሰራቸው ያለንበት ሁኔታ በምርጫ 2013 ለመሳተፍ የሚያስችል አይደለም" ሲሉ የምዕራብ ሸዋ፣ ምሥራቅ ወለጋና ኢሉ አባ ቦር ኦፌኮ ተወካዮች አቤቱታ አሰምተዋል።

የዞኖቹ ኦፎኮ ተወካዮች ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “የታሰሩት ከተፈቱ፣ ፅህፈት ቤቶቻቸው እንዲከፈቱ ሁኔታዎች ከተመቻቹ፣ የዲሞክራሲ ምህዳሩ ከሰፋና ያላንዳች ማስፈራሪያና ዛቻ መንቀሳቀስ ከቻልን በምርጫው ለመሳተፍ አያዳግተንም” ብለዋል።

የዞኖቹ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤቶች ኃላፊዎች ደግሞ "የኦፌኮ ተወካዮች ቅሬታ መሰረተ-ቢስ ነው” ብለዋል።

የታሰረ የኦፌኮ አባልም ሆነ የአመራር አባል በዞኖቹ ውስጥ እንደሌለና በብልፅግና ፓርቲ ተፅዕኖ የተዘጋም ፅህፈት ቤትም አለመኖሩን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።


XS
SM
MD
LG