በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ አስቸኳይ እርዳታ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ በደቡብ ሱዳን የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ አሌይን ኑዴሁ
ፎቶ ፋይል፦ በደቡብ ሱዳን የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ አሌይን ኑዴሁ

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ስድስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች መርጃ የሚውል የአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር አስቸኳይ እርዳታ ተጠየቀ።

ይህን አጣዳፊ እርዳታ ተማፅኖ ያቀረቡት በደቡብ ሱዳን የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ አሌይን ኑዴሁ ሲሆኑ መስሪያ ቤታቸው እአአ 2021 ለደቡብ ሱዳን የምግብ እና ሌሎችም ችግሮች ያዘጋጀውን ምላሽ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛው የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ በበኩሉ በተለያዩ አጎራባች ሃገሮች ለተጠለሉ ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች መርጃ የሚውል የአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተማጽኗል።

XS
SM
MD
LG