በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒው ዮርኩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ሰልፍ …


ትውልደ ኢትዮጵያ-አሜሪካውያን በትናንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ካኪያሄዱት ሰልፍ
ትውልደ ኢትዮጵያ-አሜሪካውያን በትናንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ካኪያሄዱት ሰልፍ

“ዩናይትድ ስቴትስ እና የተቀረው ዓለም ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የት ነበራችሁ? ኢትዮጵያውያን በግፍ ሲገደሉ፤ ሲዘረፉ: በሺዎች ሲገፉ እና ለስደት: ለእንግልት ሲዳረጉ የት ነበራችሁ?” በሰልፉ ላይ ከተሰሙ ድምጾች እና መፈክሮች ውስጥ ናቸው።

“ሁሉም ወገኖች .. አሰምርበታለሁ .. ሁሉም ወገኖች ውጊያውን አቁመው ይህ ሰው ሰራሽ ሰብዓዊ ቀውስ እልባት ያገኝ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጥሪ እናቀርባለን።” አምባሳደር ሊንዳ ግሪንፊልድ።

“በሃሰት መረጃ ተመስርቶ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመጻረር የሚደረጉ ጫናዎች ይቁሙ!” የሚል መልዕክት ያነገቡ ከኒው ዮርክ እና አጎራባች ግዛቶች፤ እንዲሁም ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው የተጓዙትን ጨምሮ በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በትላንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያ-አሜሪካውያን በትናንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ከአካሄዱት ሰልፍ
ትውልደ ኢትዮጵያ-አሜሪካውያን በትናንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ከአካሄዱት ሰልፍ

በኒው ዮርክ ከተማ የሚገኙትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የኒው ዮርክ ታይምስ ዋና መሥሪያ ቤቶች ደጃፍ ጨምሮ በተለያዩ የከተማይቱ አደባባዮች ስለተካሄደው ትዕይንተ-ሕዝብ ካስተባበሪዎቹ አንዱን ሰልፎቹ እየተካሄዱ በነበረበት ሰዓት ካሉበት ስፍራ በስልክ አነጋግረናል።

በሌላ ዜና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የተካሄደውን ስብሰባ የመሩት የጸጥታው ምክር ቤት የወሩ ሊቀ መንበር የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ ተጠሪ አምባሳደር ሊንዳ ግሪንፊልድ በሰጡት አስተያየት “በትግራይ የተካሄደው ጦርነት ንጹሃን ዜጎችን ከከፋ አደጋ አፋፍ አድርሷል። የምግብ ክምችት ተሟጧል። ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት አደጋም እየመጨረ ነው። እየተካሄደ ያለው ግጭት ሠብዓዊ እርዳታ ለተቸገሩ ወገኖች በአፋጣኝ እንዳይደርስ እንቅፋት ፈጥሯል” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኒው ዮርኩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ሰልፍ …
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00


XS
SM
MD
LG